ወሎ የኢትዮጵያ ውርሰቅርስ ማህበር

Wollo Ethiopian Heritage Society

P. O. BOX 4301 • PORTLAND • OR 97208 (USA)  wollo.org; wolloheritage.net

******************************************************

ድርጅታዊና ትምህርታዊ መግለጫዎች፦

======================================================

 

==================

የሕብረት መግለጫ፦

በዋሽንግተን ዲሲ ስለተደረገው የክፍለሃረራት ሕብረት ጉባዔ

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

==================

PRESS RELEASE ON RECENT EVENTS IN NORTH WOLLO

(Click here for full text)

 

ስለ ሰሜን ወሎ ጭፍጨፋ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ

(ለማንበብ እዚህ ይርገጡ)

 

==================

ስለወልድያ ከኢትዮጵያ ክፍለ ሃገራት ሕብረት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

January 20, 2018

 

===================

ከ«ወሎ ውርስና ቅርስ» ስለ ወቅታዊ የወሎ ሁኔታ የተሰጠ መግለጫ

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

December 13, 2017

=========================

ከኢትዮጵያ ክ/ሃገሮች ማህበራት የተሰጠ የጋራ መግለጫ

(Press on the above title to open the PDF)

November 4, 2017

 

======================

September  24, 2017

Analysis:  For the full document, click on the title below (የበታቹን አርእስት ይጫኑ) ....

World Bank, Spatial Development in Ethiopia

አለም ባንክ፦ በወረዳዎች መካክል ያሉት የእድገት ልዩነቶች በኢትዮጵያ

 

=======================

 

Press Release: 

September 5, 2017

 The Unnoticed 2017-18 Ethiopian Famine is Well Underway

Let us join hands to make famine history!

 

Millions of people in the Horn of Africa are currently facing acute food and water shortages on the heels of a major food crisis in 2015-16.  Whatever the precipitating causes (drought, global warming, etc.), the underlying cause is the unwillingness of sitting governments to guarantee food security in slowly-developing famines become a clear and present danger.

International humanitarian agencies have issued appeals for emergency relief to save some 8.5 million Ethiopians (especially those residing in the lowlands) and millions more East Africans are on the verge of starvation.  Hundreds of thousands have already become internally displaced in search of food and water.  The world seems to suffer aid fatigue while a disastrous humanitarian situation is rapidly deteriorating, including tale-tale signs that the next rainy is season will also fail.

The world has made a remarkable progress over the past 25 years.  Millions of Ethiopians are among the one billion people lifted out of debilitating poverty.  National and regional famines that claimed the lives of millions in South Asia and Sub-Saharan Africa are thankfully a thing of the past, save the most an unpredictable natural catastrophe. We can eliminate this scourge from Africa, too.

To understand why Ethiopia remains so vulnerable to chronic hunger and premature death even in normal years, one needs to keep the following facts in mind:

·         Ten percent of Ethiopia’s 100 million people endure chronic hunger (under-nutrition and malnutrition). Millions more live just above this precarious subsistence line even in years of normal rainfall.

·         Famine-level situations, which used to occur every ten years, are now occurring every couple of years or so.  Despite claims of rapid economic growth, rural livelihoods in Ethiopia’s arid pastoral southeastern lowlands are becoming unsustainable.

·         While we are grateful for the tireless rescue operations of international charities, the primary responsibility of saving the lives of its citizens falls squarely on the shoulders of the Ethiopian regime. We are indeed offended by the insinuations of high government officials that it is ultimately the responsibility of the international community to deal with food shortages.

It is our sincere belief that famine-related deaths and morbidity constitute an egregious violation of the mother of all human rights—the right to live.   Furthermore, drought may be unavoidable, but famine is an eminently avoidable tragedy.  No self-respecting democracy has ever allowed its citizens to suffer and die in such numbers and for so long.   

Wollo Ethiopian Heritage Society, therefore:   

1.         Calls on the Ethiopian Government to stop playing politics by using starving people as an excuse for begging and instead devote all its resources to save the most vulnerable population; 

2.      Calls on the international community to once again provide generous and timely aid instead of waiting for large-scale deaths as “proof of need.” We also implore donors to insist on sensible food security policies that would make such recurrent dependency on food aid totally unnecessary for a country that has a great potential to feed itself; and

3.       Implores Ethiopians and friends of Ethiopia in the Diaspora of any political persuasions to extend a generous helping hand through famine relief organizations of their choice.  

Thank you.

WEHS:  wollo.org

==============================

August 30, 2017

የወያኔ መንግስት የሰሜን ጎንደር ዞንን ለመከፋፈልና የምዕራብ ጎንደርን መሬት ለመቀራመት ያወጣዉ እኩይ እቅድ አገር አጥፊ ነው!

በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እንድምንሰማዉ የወያኔ አስተዳደር የሰሜን ጎንደር ዞንን ለሶስት ለመክፈል እንደወሰነና ለዚህም ምክንያቱ ላለፉት 26 አመታት ለልማት ምቹ ስላልሆነ ነው የሚል ነዉ። የአማራን መሬቶች የትግራይ ለማድረግ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአማራና ቅማንት ማኅበረሰብ ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው 12 ቀበሌዎች ሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ እየተዘጋጀ ነውም ተብሏል። ይባስ ተብሎ የ“ታላቋ ትግራይን” ሕልም ለመተግበር ሕወሃቶች ጎንደርና ጎጃም ከሱዳን እንዳይዋሰኑ ለማድረግ ትግራይን እስከ ጋምቤላ ለማስፋፋት ያዘጋጁት ሚሥጥራዊ ካርታ በቅርቡ ይፋ ወጥቶ ለማየት በቅተናል። 

ቅማንትና አማራ በሚለዉ ክፍፍል ያልሰራለት ወያኔ አሁን ደግሞ ለ3 ዞን ከፍሎ የሰሜኑን ጫፍ ወደ ትግራይና ሱዳን፣ መካከሉን ቅማንት ለሚባል ከዋናዉ ወገኑ የተለየ በግጭት ሁልጊዜ የሚኖር አካባቢ ለመፍጠር፣ ሶስተኛዉ የአማራ ዞን በማለት 3 እርስ በእርሳቸዉ እንደ እስራኤልና ፍልስጥኤም ዘወትር በስጋት የሚኖሩ ማህበረሰቦችን በመፍጠር ጎንደሬን እርስ በእርሱ በማስተላለቅ ወያኔ የቀበሮ ዳኛ የሚሆንበትን ስርአትና ሁኔታ ምቹ ለማድረግ የታሰበ ስንኩል እቅድ መሆኑ ግልጽ ነው። የመሬት ቅርምቱም ስልጣን ካጣን ትግራይን ነጻ እንገነጥላለን ከሚል ቅዠት የመነጨ ነው።

ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት እንደሚባለዉ፣እስካሁን በአካባቢዉ ምንም አይነት ልማት ያልተካሄደዉ አካባቢዉ ስላልተከፋፈለ ሳይሆን ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ ባለዉ የተንሸዋረረ አስተሳሰብ ምንም አይነት ልማት ወደ አካባቢዉ እንዳይሄድ ስላደረገ ነዉ። በወልቃይታና በጠገዴም የታየው የዘር ማጽዳት፣መሬት መቀራመትና፣ የአማራን ማንነት አትፍቶ በትግሬ ማንነት ለመተካት የተፈጸመው ድርጊት የዚህ ታላቅ ሴራ ሌላው ምልክት ወይንም መንስዔ መሆኑን ማንም አያጣውም።

የሕዝብ መከፋፈልና መሬት መቀራመት የሚያለማ ቢሆንማ ገና በጥዋቱ ወሎን ለ6 ከፍሎት አልነበር እንዴ? ወሎን ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ ከሚሴ፣ አፋር፣ ዋግ ህምራ እና ወደ ትግራይ ቆርሶ የወሰደዉ ራያን በመሸንሸን አንዱ ላንዱ ችግር እንዳይደርስ አድርጎ አዳክሞ ምንም አይነት መሰረተ ልማት እንዳይደርስ በማድረግ አዳክሞ ወደ መጥፋት ደረጃ አድርሶታል።

ሁላችንም በየግቢያችን ችግሩን ተረድተን አብሮ ለመስራት ተስፋ እየታየ በመሆኑ ጎንደሬዎች በህብረት ቁማችሁ የምትታገሉበት እንጂ የምትለያዩበት ወቅት አይደለም። ከድል በኋላ ራሳችሁ ቁጭ ብላችሁ እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎች ወንድሞቻችሁ በተገኙበት ችግራችሁን እስከምትፈቱበት ጊዜ ድረስ በትእግስትና  ነገሮችን በጥሞና ማየቱ እጅግ አስፈላጊ ነዉ። የገዢው ፓርቲ ደባም ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በቀጥታ የሚመለከት ነው።

በኛ አስተያየት የጎንደርና የወሎ ሕዝብ በደም፣ በባህልና በታሪክ መንታ ነው። ከዚያም በላይ ኢትዮጵያዊነታችን ያስተሳስረናል። ስለዚህ ወሎ የኢትዮጵያ ዉርስና ቅርስ ማህበር ከጎናችሁ በመሆን ትግሉ የሚጠይቀዉን መስዋእትነት አብሯችሁ ለመክፈል ዝግጁ ነዉ።

ያገር አድን ክተት ጥሪ ለሁላችንም ነው!!

ድል ለተባበረው የኢትዮጵያ ህዝብ!!

======================

August 9, 2017

የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚታገለው ለመሠረታዊ የሥርዓት ለውጥ እንጂ ለሽርፍራፊ ጥቅም አይደለም!

ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ሕዝብን እርስ-በርሱ ለማጋጨትና ለማጫረስ በማሰብ በየወቅቱ የቀውስና የችግር አጀንዳ ከማውጣት ቦዝኖ የማያውቀው የጎሠኞች ስብስብ የሆነው ወያኔ መራሹ ቡድን በተለመደ መሠሪ ባኅሪው እነሆ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሁለት አገር የሚያናጉ የጥፋት መንገዶችን ቀይሶ ሕዝባችንን ወደ ትርምስ እየገፋው ይገኛል።

በመጀመሪያ ‘አዛኝ ቅቤ አንጓች’ እንዲሉ የኦሮሞውን ማኅበረሰብ ጥቅም በማስከበር ስም፣ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ትብብር፣ እውቀት፣ ገንዘብ፣ ላብና ደም የተቆረቆረችውን የጋርዮሽ ጥንታዊት ከተማ፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊ መኖሪያ ቤት፣ የአፍሪቃና የዓለም-አቀፍ መድረክና መዲና የሆነችውን አዲስ አበባ፣በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም በሚገኝ ብድርና እርዳታ ከዘረፋው በተረፈው፣ ነገ ለእዳው ሁሉም በሚጠየቅበት ገንዘብ በማደግ ላይ ያለችውን ከተማ ለአንድ ነጠላ ማኅበረሰብ ብቸኛ ንብረት አድርጎ ያቀረበው ተንኮል ባሰበው መልክ ፍሬ ባለማፍራቱ እንደለመደው ወደ ሌላ የግጭትና የቀውስ ምክንያት ማተኮር ግድ ሆኖበታል። በየወቅቱ እንደ አለላ ሰበዝ እየመዘዘ ከሚያወጣቸው የቀውስ ስልቶች ውስጥ ሰሞኑን ያወጣው ከሕዝብ አቅም ውጭ የሆነው የግብር (የዘረፋ ማለት ይቀላል) ግዴታ ነው። ምንም እንኳ አገዛዙ ከፍተኛ የገንዘብ ችግር እንዳለበት ቢታውቅም፣ በግብር ክፍያ ስም የተጫነው የዕዳ ቀንበር ዓላማ ግን ይኽም ሣይጨመር እጅግ ከባድ የሆነው የኑሮ ውድነት ጨርሶ ከአቅም በላይ እንዲሆንና ሕዝብ ለመብቶቹ መከበርና ለሥርዓት ለውጥ የሚያደርገው የወያኔ በቃኝ የእንቢተኝነት ትግል ላይ ያለውን ትኩረት ለማስቀየር ተብሎ የተሰላ ከመሆን አያልፍም።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አምናም ሆነ ታች-አምና፣ ትናንትም ሆነ ዛሬ ጥያቄው አንድና አንድ ነው።የሥርዓት ለውጥ ይደረግ፣ የሰብአዊና የዜጋ መብት ይከበር፣ የጎሣ ፖለቲካ ይወገድ፣ ሕዝብ አይፈናቀል፣ የኢትዮጵያ አንድነትና ዳር ድንበር ይከበር የሚሉትን ያቀፈ የዲሞክራሲ ጥያቄ ነው። ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ለመብቶቹ መከበር የሚታገለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄዎቹ ሙሉ ለሙሉ ሳይመለሱለትና ተግባራዊ ሳይሆኑለት በጥቃቅን የጥገና ለውጥና ሽንገላ ትጥቁን አይፈታም። እስካሁን ድረስ በተለመደው ጨዋነቱ ታግሶ የኖረው ሕዝብ ወያኔና ግብረ-አበሮቹ ጥያቄዎቹን ይመልሱልኛል የሚል ብዥታ የለውም። ሥርዓቱ ያመጣው ቀውስ በሥርዓቱ መወገድ ብቻ እንደሚጠናቀቅ ያውቀዋል።

ይኽንን ቅጥ ያጣ የግብር ጫና ተከትሎ በየክፍለ-አገሩ (በተለይም በሸዋ፣በወሎ፣ በጎጃምና በጎንደር) የሚታየው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ግብር ይቀነስልኝ ብቻ ሣይሆን ለአልጠግብ-ባይ ዘራፊ መንግሥት ነኝ ባይ ጎሠኛ ስብስብ እራሴ በጥይት ለምደበደብበት፣ ለምታሰርበት፣ ለሚያሳድደኝ ሥርዓት ዕድሜ ማራዘሚያና ለሰቆቃዬ መቀጠል  ግብር አልከፍልም እምቢ! የሚል መሆን አለበት። የጥገና ለውጥን መቀበል የጨቋኝ መንግሥታትን ዕድሜ የሚያራዝምና በሕዝብ ላይ የሚያደርሱትን አፈና እና ጭቆና ይበልጥ በከፋ መልኩ እንዲቀጥሉበት የሚያደፋፍራቸው እንደሆነ መታወቅ አለበት።

"የነብር ጅራት አይዙም ከያዙም አይለቁም" ነውና ነካክቶ ሥር-ነቀል ለውጥ ሳይመጣ ተደልሎና ተሸንፎ ማፈገፈግ ለበለጠ እልቂት ይዳርጋል። የዛሬ አርባ ሦስት ዓመቱን የየካቲቱን የተያያዘ ሕዝባዊ ትግል እንደ አርአያ በመውሰድ ብሎም ተጨናግፎ የሌሎች ተመሳሳይ ቡድኖች የሥልጣን መወጣጫ ክፍተት እንዳይኖር በተቀናጀ መልኩ አሁን የተቀጣጠለው ሕዝባዊ እምቢተኛነት ሥርዓቱ ተንበርክኮ እስኪወገድ ድረስ መቀጠል አለበት። የሕዝባዊ ትግሉ አገር-አቀፍ ባኅሪና ብሔራዊ ይዘት እንዲኖረው ተአማኒነት ያለው አስተባባሪ አካል በአስቸኳይ መቋቋም እንዳለበት ልናሳስብ እንወዳለን። ያልተያያዘና በጋራ ያልተመራ ትግል ለመሰናከል ያለው ዕድል ከፍተኛ ነው። የጋራ አመራሩም ከጎሠኝነት የፀዳ፣ በኢትዮጵያዊነት ላይ ያረፈ መሆን ይኖርበታል። በዛ ካስማ ላይ ያረፈን ኃይል ደፍሮ የሚያነቃንቀው አይኖርም። 

ወሎ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር ከሌሎቹ ተመሳሳይ ማኅበራት፣ ማለትም ከጎንደር ኅብረት ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ከጎጃም ዓለም-አቀፍ ማኅበርና ከሸዋ ሁለገብ ማኅበር ጋር በመተባበር ሕዝቡ የሚያደርገውን ያላሰለሰ ትግል በማድነቅ ወደፊትም ለጥገና ሣይሆን ለመሠረታዊ ለውጥ ተባብሮ እንዲነሳ ድጋፍ ለማበርከት በአንድነት መቆማችንን ልናበስር እንወዳለን። በመደራጀት ላይ ያሉት የሌሎቹ ክፍለ-አገር ተወላጆች ማኅበራት ወደ መድረክ ሲመጡና በጋራ መቆም ሲችሉ የተጀመረው አገር-አድን እና የሥርዓት ለውጥ ሕዝባዊ ትግል ላይ የሚኖረው አዎንታዊ አስተጋብዖ ቀላል አይደለም።

በዚኽ መልክ የሚካሄደውን አገር-አቀፍ ትግል ለማደናቀፍ ወያኔና መሰሎቹ እንደማይተኙ የታወቀ ነው። በእኛ በኩል ግን ላለመጠለፍና ትግሉ እንዳይከሽፍ የሚቻለውን ጥንቃቄ እናደርጋለን፤ ሕዝቡም ለአፍራሽ ዘመቻዎችና ቅስቀሳዎች ጆሮና ትኩረት እንዳይሰጥ ከወዲሁ አደራ እንላለን። ኢትዮጵያ የክፍለ-አገሮች ድምር ውጤት ስለሆነች በየክፍለ-አገሩ የሚካሄደው ትግል በውስጣቸው ከሚኖሩ በርካቶች መኻል አንዱን ጎሣ ብቻ የሚመለከት ሣይሆን ኗሪውን ሁሉ ያካተተ ስለሚሆን የድል ዋስትናው ከፍተኛ እንደሚሆን እናምናለን።

ለኢትዮጵያ አንድነትና ለተሻለ ሥርዓት በአንድነት እንቁም!

ነሃሴ 3 2009 ዓ/ም

  =====================

የአምስቱ ክፍለ-ሃገራት ድርጅቶች ሲያትል ከተማ ላይ የሰጡት የጋራ ሕዝባዊ መግለጫ

(ጁላይ 6፣ 2017)

ሙሉ ሰነዱን ለማንበብ ይችን አንቀጽ ይርገጡ ...

=======================

ከወሎ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር የተሰጠ የመተዋዎቂያ መግለጫ

(Seattle, WA, USA July 6, 2017)

 

ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን፦

በመጀመሪያ ራሳችንን እንድናስተዋውቅ ለተሰጠን መልካም እድል ታላቅ የክብር ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ወሎ ለአትዮጵያ አንድነትና ነጻነት ምሰሶና ማገር የሆነ፣ ብዙ አገር መሪዎችን፣ የጦር አበጋዞችንና አርበኞችን፣በተለያዩ የእውቀት መስኮች እውቅ ምሁራንና ሊቃውንትን ያፈራ፣ ለብዙ ኪነት፣ ባህልና ታሪክ ምንጭ፣ የክርስትናና የእስልምና እምነቶች ማበቢያና  መንደርደሪያ የሆነ ክፍለ ሀገር ነው። ወሎ ዛሬ በሁለቱ ታላቅ ሃይማኖቶች እኩል-ለኩል የተከፈለና ከ95% በላዩ ደግሞ በአማራነት ራሱን ያስመዘግገበ ህዝብ ነው።

የዚህ አካባቢ ተወላጅ የሆነ ሁሉ በጋራ የሚጋራው ነገር ቢኖር ኢትዮጵያዊነቱን አክብሮና ተቀብሎ ከቀረው ኢትዮጵያዊ ጋር በፍቅርና በሰላም፣ዘር፣ ቋንቋ፣ ክልልና እምነት ሳይገድበው ተዋልዶ  ህብረብሄር የሆነ ቤተሰብ መስርቶ በሄደበት ከሚኖረው ጋር በታታሪነቱ ተከብሮና ተከባብሮ መኖሩ ነው።

ወሎ የተለያዩ ማህበረሰቦች በአንድ በአማርኛ ቋንቋ እየተግባቡ ባህሎቻቸውን ተወራርሰው በሰላም የሚኖሩበት ክፍለሃገር በመሆኑ ትንሿ ኢትዮጵያ ተብሎ ሲሰየም የህዝቡን ደግነትና ሁለገብነትንም ለመግለጽ ሲባል «ወሎ ገብሱ»የሚል ቅጥያ ተሰጥቶታል።ገብስ ለጤና ተስማሚ፣ ለተለያዩ ምግብና መጠጦች ዝግጅት ቀዳሚ ቦታ እንዳለው ሁሉ፣ የህዝቡንም ሰላማዊና የልዩ ልዩ ችሎታ ባለቤት መሆኑን ለመግለጽ ሲባል የተሰጠ ስያሜ ነው። ይህንንም ለመግለጽ የገብስ ቡቃያን የማህበራችን ልሳን ተጨማሪ አርማ (ሎጎ) አድርገነዋል።

1.  አመሰራረት መንሰኤዎች

ምንም እንኳ ወሎ ብዙ የኢትዮጵያ መሪዎች የበቀሉበት አካባቢ ቢሆንም በተለያዩ ጊዜዎች በአገራችን ላይ የሰፈኑት ስርዓቶች ትኩረት ያልሰጡትና ለተለያዩ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ጉዳቶች የተጋለጠ መሆኑ አይካድም።ለዘመናት ተደጋጋሚ የድርቅ አደጋ ክስተት የብዙ ህዝብ ህይወት ጠፍቷል፤በቀላሉ ሊወገዱ በሚችሉ በሽታዎች ሰለባ ሆኗል።ለእድገትና ለውጥ ሳይበቃ ለችግርና ለስደት ተጋልጧል።

ይህን ሁሉ ችግር ተሸካሚ የሆነውና ከ8 ሚሊዮን በላይ የሚገመተው የወሎ ህዝብ ግን ብሶቱን ችሎ በተለያዩ አስተዳደሮች ላት ያለው ቅሬታ ሳይገታው የአገሩ የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ሲደፈር እንደ ንብ አውራ ግንባር ቀደም ሆኖ ለአገሩ ክብርና ነጻነት አንድ ህይወቱን አሳልፎ የሰጠው ቁጥሩ ቀላል አይደለም።ለወደፊቱም መስዋእት ለመሆን አላመናታም።ወደፊትም አያመ

አሁን በስልጣን ላይ የተቀመጠው ቡድን መሪ የሆነው የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት (ህወሃት) ገና ከጅምሩ ጫካ የገባው ኢትዮጵያን ለማጥፋትና የትግራይንና የኤርትራን ክፍለ-ሃገርር ገንጥሎ ነጻ መንግስት ለማቋቋም በመሆኑ ለዚያ እቅዱ  እንዲመቸው መጀመሪያ ያነጣጠረው በኢትዮጵያዊነት ጠንካራ አቋም ያላቸውን ማህበረሰቦችና አካባቢዎች በተለይም አማራውን ማዳከምና ከተቻለም ማጥፋት ነው።ለዚያም  አማራው የሚኖርበትን ለም መሬት እየነጠቁ ማፈናቀል፣ለመብቱ የሚቆመውን ድራሹን ማጥፋት፣ የምጣኔ ሃብት ምንጭ የሆነው  የተፈጥሮ ሃብት እጥረት እንዳይኖር ከአጎራባች ክፍላተ ሃገሮች ለም የሆኑ መሬቶችን መንጠቅ በእቅድ የተያዘና በተግባር የተተረጎመ ስልት ነው። አማራውን ለዘመናት በሰላም አብሮ  ከኖረው ማህበረሰብ ጋር በጅምላ ኮንኖ ማጋጨትና መነጣጠል የአምባገነናዊ አገዛዝ ስልት አድርጎ ተጠቅሞበታል፤አሁንም እየተጠቀመበት ይገኛል።

ወሎ የአፋሩ፣የኦሮሞው፣የአማራው፣የትግሬው፣የአርጎባው፣የአገዉ ማህበረሰብ፣ሃይማኖትና ቋንቋ ሳይለየው በአንድ የጋራ ቋንቋ በአማርኛ እየተግባባ ለዘመናት ተከባብሮና ተቀላቅሎ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ  የሚኖርበት ሁኔታ ለወያኔ ዓላማ አመቺ ባለመሆኑ በመብትና በእኩልነት ሽፋን  እርስ በርሱ እየተጋጨ እንዲዳከም በልዩ አስተዳደሮች እየሸነሸነ  የማለያየቱ ስልት በወሎ በጎንደርበጎጃም፣በሸዋና በቀሩትም የኢትዮጵያ ክፍለ-ሃገሮች የታዬ ሃቅ ነው።የዚህ እያናቆርክ-ግዛው ስልት የርቀት ውጤቱ  ሁሉንም የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው። የሚያስተሳስሩንን ብሄራዊ ተቋሞች (ማለት ት/ቤቶች፣የመከላከያ ሰራዊት፣ የሃይማኖት ተቋሞች፣ የጋራ ቋንቋዎች፣ ወዘተ) በማመንመን ከኢትዮጵያዊነት ማንነቱ አልፎ የመኖር ህልውናውን የሚያጠፋ ከባእዳን ሴራ ጋር የተቆራኘ ተንኮል መሆኑ ቁልጭ ብሎ እየታየ ነው

አሁን በኢትዮጵያ የስልጣን አጎበር ላይ አድርጎ የተቀመጠው ወያኔ-መራሹ ቡድን በተለይም በጎንደርና በጎጃም ውስጥ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ አመጽ ለማዳፈን ወሎን የመተላለፊያና የጦር ማከማቻ አድርጎ ለመጠቀም የሚያደርገው ሙከራ በህዝብ መካከል ሊፈጥር የሚችለውን ቂም በቀል ጥላቻና ቅርሾ በማጤን ያንን  ለማክሸፍ ፣ከሚንቀሳቀሱት ወግኖቻችን ጋር በመቀላቀል የሕዝባዊ እምቢተኛነት ትግሉ ምህዳር ሰፍቶ አገር አቀፍ እንዲሆን ካለን ምኞትና ፍላጎት በመነሳት ይህንን ማህበር አቋቁመናል።

የወሎ ተወላጅ በዚህ ስርዓት የተጎዳ፣መሬቱን ተነጥቆ የተፈናቀለ፣ወጣቱ ተሰዶ በየአረብ አገር የባርነት ኑሮ የሚገፋ፣ክብርና ስብእናውን ያጣ በመሆኑ ተደራጅቶ ከመታገልና  መብቱን ከማስከበር የተለየ አማራጭ የለውም።መፈናቀሉን፣መሰደዱን፣መታሰሩን፣መገደሉን ሁሉም ወሎዬም ሆነ የተቀረው  አትዮጵያዊ ሁሉ በጋራ የቀመሰው ጉዳት ነው።እርግጥ በአማራው ማህበረሰብ ላይ ጥቃቱ ቢበረታም፣ በተመቸው መንገድ ተደራጅቶ ራሱን የማዳን መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ይህ አምባገነንነት ለእሱ ብቻ የመጣ አይደለም።ይብዛም ይነስም ሁሉም በጅራፉ ተገርፏል።ይህን በመገንዘብ የጋራ ችግሩን በጋራ ትግል እንዲያስወግደው፣ ትግሉም በአንዳንድ ጮሌዎች እንዳይጠለፍና ዳግም ለተመሳሳይ የጭቆናና የጎሰኞች ስርዓት እንዳንዳረግ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተገንዝበናል

ከአንድ ዓመት ወዲህ ተስፋ የሚሰጡ ህዝባዊ አመጾች እየተቀሰቀሱ መጥተዋል።የሚቀራቸው መጠንከርና በቁልጭታዊ ራዕይና ስልት መያያዝ ብቻ ነው።በጎንደር፣በጎጃም፣በወሎና ፣ሸዋ ውስጥ ህዝባዊ ትግሉ ከጎለበተ በሌላው ክፍለ-ሃገር ውስጥ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ለሚያደርገው ትግል ፋኖስና ደጀን ይሆነዋል።ለመቀላቀልም በር ይከፍትለታል።ለዚያ ደግሞ ለውጥ ፈላጊው በተለይም በውጭ አገር የሚኖረው ዜጋ አለሁላችሁ ብሎ የአቅም ግንባታ ላይ ሲረባረብና የሚያስፈልጋቸውን ሲያበረክትላቸው ነው። ከጎሰኝነት የራቁና የጸዱ ህዝባዊ ትግሎች በማጠናከር እንዳይከስሙ ማድረጉ ቀዳሚው ስራችን መሆን አለበት ብለን እናምናለን። በኢትዮጵያዊነቱ በየእካባቢው ጥቃት የሚደርስባቸዉን ወገኖቻችንን ለመታደግና አገራችንን በጎጠኞች ከመፈራረስ  አድነን የመልካም አስተዳደር ባለቤቶች ለመሆን እንድንበቃ የግዴታ መተባበራችን ወሳኝ ነው።

2.  የወሎ ውርስና ቅርስ ተልዕኮዎች

ወሎየነት መለያችን፤ኢትዮጵያዊነት ማንነታችን” የሚለው መፈክራችን ሰፊ ምህዳርን ያቀፈ ነው። ወሎ የእትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር ነፃና ገለልተኛ እንዲሁም አለም-አቀፍ ሲቭክ ድርጅት የወሎ ትውልድ ያላቸውንና የማህበሩን  ዓላማ የሚቀበሉትን  ኢትዮጵያውያን  ሁሉ በማሰባሰብ ለወሎ ክፍለ-ሃገርም ብሎም  ለኢትዮጵያ ሃብታዊና ፖለቲካዊ እድገት አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ ማስቻል በመጋቢት 2009 ዓ.ም. የተቋቋመ ማህበር ነው

ተለዕኮዎቻችን በክፍለ-ሃገሩ ልማትና በዜጎች መብት መከበር ላይ በማተኮር “ወሎ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ፡ ማህበር 4 መርሆዎችንና ማንነቶችን ያካትታል፦

1ኛ) አካባቢያዊ ወሎየነት፦ የወሎ ሕዝብ የስርዓቱ ሰለባ እንጂ ተጠቃሚ እንዳልሆነና መሬቱን፣ማንነቱን እየተገፈፈ መኖሩን በማጤንበሃይማኖትና በቋንቋ ተለያይቶ እርስ በርሱ እንዲተላለቅ የሚያደርገውን አምባገነናዊና መሰሪ ተግባር በማክሸፍ የዜግነት ክብርና መብቱን የወሎን ሕዝብ አንድነትና የነበረውን መልካም ግንኙነት እንዲጠነክር ለማድረግ፣ የተፈጥሮና ሰው-ሰራሽ አደጋ ቢከሰት ለመርዳት፤የወሎ ግፍለ ሃገር ነባር ይዞታዎቹ ተመልሰውና የማሕበረሰቡ የኑሮ ደረጃ ተሻሽሎ፤ ክብሩና ማንነቱ ተረጋግጦ፤ እንዲሁም የወሎን ውርስና ቅርስ በማዳበርና ሕዝቡ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት ስርዓት እንዲሰፍን ለመታገልና ለመርዳት፤

2ኛ) ባህላዊ አማራነት፦ የኢትዮጵያን አንድነት ለማፈራረስ ሲባል በቅድሚያ አማራው የጥፋት ዒላማ መደረጉን በመረዳት ጥቃቱን ለመቋቋም፣ ክልልና ብሔር-ብሔረሰብ የሚሉት ቋንቋን መሰረት ያደረ የከፋፍለህ-ግዛ አጥሮችን አፍርሶ ሰው በሰውነቱና በዜግነቱ እኩላዊ መብቱ ተከብሮለትና ተከባብሮ የሚኖርበትን ስርዓት ለማስፈን የተጀመርውን ህብረ-ነገድና ህብረ-ሃይማኖት እምቢተኛ ትግል ለማገዝ፣

3ኛ) ብሄራዊ ኢትዮጵያዊነት፦  ከአያት ቅድመ-አያት የተረከብነውን ባህል፣ቅርስ፣እምነት፣ተፈጥሮ ካደለችን ሃብትና የመሬት ስፋት ጋር አስከብረን ለተተኪው ትውልድ ለማውረስ  የአገራችንን የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት ለማስከበር ተመሳሳይ አቋም ካለው ከሌላው ክ/ሃገር ተወላጅ  ኢትዮጵያዊ ጋር በአንድ ላይ መቆም አስፈላጊነቱን በማመን፣ወሎዬ በሌላው አካባቢ የሌላውም አካባቢ ተወላጅ በወሎ የመኖር መብቱን ለማስከበርአንድ ሕዝብ፣አንድ አገር፣አንድ ሰንደቅ ዓላማ የሚለውን መርሆ በተግባር ለመተርጎም

4ኛ) አለም-አቀፋዊ መብተኝነት፦ ታላቅ ታሪክ ያለው ወሎየ ህዝባችንና ሰፊ የህዝብ ጥንቅር የያዘችው አገረ-ኢትዮጵያ ስላምንና ብልጽግናን የምትጎናጸፈው በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ዘመናዊነትን ክቋሚ እሴቶቿ ጋር ስታዋህ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ስለዚስ አንዱ አላማችን በአለም አቀፍ ደረጃ የተደነገጉ የዜጎች ሰብዓዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መብቶቹ እንዲከበሩለት ሕዝቡ የማያቋርጥ ዴሞክራሲያዊ ትግል ማድረግ እንዳለበት ለማስተማርና የአለንልህ ጥብቅናም ለመቆም ናቸው።

ስለዚህ ከላይ በተዘረዘሩት ተልዕኮዎች ጋር በሚጣጣም መንገድ፡ ወሎ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበርና አለም-አቀፍ ቅርንጫፎቹ ከግቦች አንጻር 5 ነጥቦችን መጥቀስ ይቻላል፦

1.  የወል መለያችን ውሎየነት በባህሎቹ ባለጸጋ መሆኑ እንዲቀጥልና በዘመናዊነት እንዲዳብር መርሃ-ግብር አዘጋጅቶ መስራት፣

2.  በአማራነታቸውና በኢትዮጵያዊ ማንነታቸው አገርም ውስጥ ሆነ እውጭ አገራት የጅምላ ጥቃትና አድልዎ የሚደርስባቸውን ወሎየዎችንና በአጠቃላይ ሁሉንም ተበዳይ ኢትዮጵያውያንን መታደግ፣

3.  ሙሉ የዴሞክራሲና ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ መሟገት፣

4.  ከሃይማኖትከጎሳ፣ከጾታ ከመደብ ክልል ፖለቲካ ጠንቅ የጸዳች ኢትዮጵያን ለመገንባት ከሚታገሉ አጋር ድርጅቶች ጋር አብሮ መስራትና፣

5.  እነዚህን አላማዎችና ግቦች በስራ ለማዋል የጠሩ ሃሳቦችን፣የብሄራዊ አጀንዳ ንድፎችን፣የሰው ሃይልንና የገንዘብን ማሰባሰብ ፕሮግራም ማውጣትና በስራ ማዋል ናቸው።

ለበለጠ ግንዛቤ በቅርቡ ይፋ የሆነውን ድረገጻችንን ይጎብኙ፣በኢሜይልና ሶሻል ሚዲያ መስመሮቻችን ይገናኙን።

 

  •  በወሎ ላይ ድህነትና ጭቆና ተደምስሠው ብልጽግናና ዴሞክራሲ ያንሰራሩ!
  •  በኢትጵያዊው አማራ ህዝብ ላይ የተከፈተው የማፈናቀልና ዘር የማጥፋት ዘመቻ ይቁም!
  •  የአገር ወዳዶች ግንባር ተመስርቶ ለኢትዮጵያዊነት ዘብ ይቁም!
  •  ትዮጵያ አገራችን በአንድነትና በነጻነት ለዘላለም ትኑር!  

 -- ወሎ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር ቦርድ።

 

 

====================================================================


 «ፈረሱም ይኸው፥ ሜዳውም ይኸው »


Become a Partner and a member of wollo heritage:

ሙሉ የአባልነትን ፎርሙን ከመግቢያው ገጽ (HOME) ውስጥ ያገኙታል።  ባጭሩም የሚከተለውን ሞልተው መመዝገቢያዊን በፖስታ ሳጥናችን ሊልኩልን ይችላሉ፡

If you wish to join as a member, please fill out the form below and send us your membership dues separately.  The detailed "Membership Form" can be downloaded from the "HOME" page and mail it to us.  Thank you!

Name *
Name
Send Checks or other Money Orders to our mailing addresses. Thank you.