What is NEW...

=====================

Press ReleaseS &

Educational Documents:-

=====

ሕዝባዊና ትምህርታዊ  መግለጫዎች፦

 • ስለ ሰላማዊ የትግል ስልቶች ትምህርታዊ ጽሁፎችን ለማንበብ  "PROJECTS" ገጽ ሄደው ይመልከቱ።

 • መግለጫዎቻችንን ሙሉ በሙሉ ለማንበብ "EVENTS" ገጽ ሄደው ይመልከቱ።

======================

ጀግናው የራያ ህዝብ እርዱን እያለ ነው፦

መቀሌ ላይ የመሸገው የትህነግ ወሮበላና ዘረኛ ሃይል የዜጋዊ ማንነቴ ይከበር ብሎ ለሰላማዊ ሰልፍ በወጣው የራያ ህዝብ ላይ ልዩ ፖሊሶቹን እንደገና አስገብቶ የገደላ፣የቁሰላና የአፈሳ እኩይ ተግባሮቹን እያጧጧፈ ይገኛል፡፡ ነጻ የትግራይ መንግስትን ለማቋቋም የሚቃዠው ነውጠኛ ቡድን በህገ-መንግስት መልክ ያሰፈረው የከፋፍለህ ግዛው ስልትና ከርካሪ ገመድ አንገቱ ላይ ሳያስበው እየተጠመጠመበት ይታያል። የሚያስገርመን የአገሪቱን ሰላም ማስጠበቅ በማይችል አስተዳደር ላይ መውድቋ ነው። ለምሳሌ ያህል የፌደራል ሰራዊት በሚያሳፍር ሁኔታ ጅጅጋ ላይ ተልኩሶ በማሸግሸግ ህዝቡን እንዳስመታው ከአለማጣም ሳይቆይ አልቻልኩም በማለት እግሬ አውጭኝ ብሏል፡፡ ህዝቡ ድረሱል እያለ ነው፡፡

ለማንኛውም በኢሳት እለታዊ ፕሮግራም ላይ (በ 10/22/2018) የተደረገውን ትምህርታዊ ትንተና የሚከተለውን ማስጠንፈሪያ ረግጠው ይስሙ፡፡

ESAT Eletawi on Raya Resistance: Oct ‘18

======================

October 14, 2018

አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ [አብን] ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ (እዚች ይርግጡ)

ከላይ በተመለከቱት ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመመርኮዝ የአብን ብሔራዊ ምክር ቤት የሚከተሉትን [ወሎን የሚመለከቱ] አቋሞች ይዟል:-

2) ያለሕዝብ ፍላጎት ከወሎ አማራ ግዛት ተቆርሶ ወደ ትግራይ ክልል በተጠቃለለው የራያ አማራ ግዛት የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዜጎችን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመማር ፍላጎት እና መብት በመገደብ የሚያደርገውን ሕገወጥ ድርጊት እናወግዛለን፡፡ በኢትዮጵያም ሆነ አገሪቱ በተቀበለቻቸው ዓለማቀፍ ስምምነቶችና ሕግጋት ሕፃናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመማር ሙሉ መብት እንዳላቸው በግልፅ ተደንግጎ የሚገኝ ነው፡፡ ይህ በሆነበት ሁኔታ የራያ አማራ ተማሪዎች ተገደው ያለፍላጎታቸው በትግርኛ ቋንቋ እንዲማሩ የትግራይ ክልል መንግስት የሚያደርገውን ያልተገባ ድርጊት በፍጥነት እንዲያቆም እንጠይቃለን፡፡ ፌዴራል መንግስቱም ጣልቃ በመግባት በራያ አማራዎች ላይ የሚደርሰውን በደልና ግፍ በፍጥነት እንዲያስቆም እንጠይቃለን፡፡

4) በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እና በጣና ኃይቅ ኃብቶቻችን ላይ እየደረሱ ያሉ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ውድመቶች በእጅጉ ያሳስበናል፡፡ የፌዴራሉ መንግስትና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ በመውሰድ ኃብቶቻችንን እንዲታደጉ በጥብቅ እንጠይቃለን፡፡

======================

 • ለዘብተኛው/አዝጋሚው መንግስት ሲያንቀላፋ የፖለቲካ ሽፍቶች በማናለብኝነት ስልጣንና መሬት ለመቀራመት የዘር ጭፍጨፋ እያደረጉ ነው፡፡ ወደ ህዝብ-ለህዝብ ጦርነትም አገሪቷን እያመሯት ነው፡፡

 • አዲስ አበባን፣ ናዝሬትን፣ ድሬዳዋን የመሰሳሉት የመላ ኢትዮጵያዊ መዲናዎችን ካረመኔዎች ያልተከላከለ ለይስሙላ ሰንደቅ ከሚሽከም የኮረፌ ጋን ቢያዝል አያምርበትም??

አገሪቷ የገጠማትን የዘረኛ መሪ መተካካት አደጋ ለመረዳት ይህን አስተማሪ ትንተና ያንብቡ፡፡

Zecharias Zelalem, “The Privatization of Violence: Why Chaos is Making a Comeback in Abiy’s Ethiopia,” Addis Standard, September 21, 2018.

<< It is now becoming clear that this “privatization” of violence has opened the doors to anyone, with access to weapons, the freedom to kill. Talk of reconciliation and democratizing the state can bear fruit only if a degree of normalcy is maintained nationwide. If unchecked, Prime Minister Abiy Ahmed’s lackadaisical approach to domestic security will be his downfall… It’s high time “Team Lemma” put niceties to the side and put a foot down.  >>

READ FULL ARTICLE …

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

የራያ ሕዝብ መብታችን-ይከበር ጥያቄ:-

ወሎየ አማራ ነን፣ነፃ ኢትዮጵያዊያን ነን!!

*** የራያ ሕዝብ የጠየቀዉ ራስን-በራስ የማስተዳደር መብቱን፣ የተረሳውን እድገቱንና፣ በተለይም በጉልበት የተቀማዉን የታሪክ ማንነቱን ነዉ!! ***

ነሓሴ 23፣ 2010 ዓ.ም.

 (August 28, 2018)

Click here to read the full text.

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

ራያ፣አለማጣ፣አዘቦ፣አበርገሌ፣ ኮረም፣ አሸንጌ

ሁሉም ወሎ ናቸው፡፡ በወያኔ የጠለፋ ግዛት የደረባቸውን ግፍና በቅርቡ የተቀጣጠለውን የአርነት ትግላቸውን ለመገንዘብ ይችን መንደርደሪያ ይመልከቱ፡፡  Blogs (ጦማር) ገጽ ሄዳችሁ ሙሉውን አንብቡ፡፡ (August 18, 2018)

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

አዲስ ጦማር ከአቶ አገሬ አዲስ፦ (June 28, 2018)

"ከጭፍን ድጋፍ ገንቢ ነቀፋና ትችት ይመረጣል!"

Blogs (ጦማር) ገጽ ሄዳችሁ ሙሉውን አንብቡ፡፡

~~~~~~~~~~~~~~~~

Ethiopian Government: Stop the escalating attacks on the Amhara, Amnesty international, June 8, 2018.

 

Editorial Note:

A.I. finally noticed the ongoing waves of ethnic cleansing of the Amhara (mostly Wolloye) from various regional states:  Beni Shangul-Gumuz, Wollega, and Illubabor.  What is most distressing is that the mass displacement of longtime residents and the confiscation of property in Qellem (Wollega) were organized in close cooperation with local OPDO officials to appease the Qeerro who we hear flipped the ill-gotten land for money.  This means, the youth protesters in some parts of the so-called Oromia Regional State are as much gripped by ethnic hatred and land grabbing as by freedom and solidarity with the Fano. Unless and until the Oromo, Somali, and Beni Shangul politicians learn to observe the rule of law and stop playing the ethnic card, there will be no united national movement for democracy.  The dislocation of 1.5 million Oromo and Somali, the Guji-Gedeo conflict (both of which were fond of dislocating the Amhara), the Sidama-Wolayta conflict in Awassa, the annexation of Amharaland (Raya, Wolqait-Tsegede-Humera, Metekel, etc.), the settlement of Tigreans and Nuers on the ancestral lands of the Afar, the Anuak, and the Amhara to change "the facts on the ground," and the renewed communal conflict in Dire-Dawa all teach the greedy victimizers the sobering lesson that ethnic cleansing is nothing but stupidly playing with fire--the cleansers will surely become the cleansed sooner than later.  A decent government will fully compensate the victims of the past 27 years of government-orchestrated violence and pillage, restore the rightful owners to their villages and neighborhoods, replace group rights by individual rights, and reject the idea of local referenda on the basis of rigged population settlements cynically organized by the TPLF/EPRDF regime.  Let's remove this political cancer before it consumes the entire body politic!!

Source of the story:

https://www.amnesty.org/en/latest/news/2018/06/ethiopia-government-must-protect-victims-of-escalating-ethnic-attacks/

 

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

የተሳካ ስብሰባ!

የካቲት ፳፭ ቀን ፪ ሽህ ፲ ዓም (March 4, 2018)

ከስድስት ወራት በፊት (ጁላይ 6 ቀን 2017) በሲያትል ከተማ በአምስት የኢትዮጵያ ክፍላተ-አገር ማኅበራት፣ ማለትም በጎንደር ኅብረት ለኢትዮጵያ አንድነት፣ በሸዋ ሁለገብ ማኅበር፣ በወሎ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር፣ በጎጃም ዓለም አቀፍ ማኅበርና በሲዳሞ ማኅበረሰብ ተመሥርቶ አሁን ሌሎቹንም ክፍለ-አገሮች እያጠቃለለ የመጣው የኢትዮጵያ ክፍላተ-አገር ኅብረት የመጀመሪያውን ስብሰባ በዋሽንግተን ዲ.ሲ. የካቲት ፲፰ ቀን ፪ ሽህ ፲ ዓ/ም (25-02-2018) ብዙ ታዳሚ በተሣተፈበት መልኩ በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል . . .

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

Wollo Heritage Society: 

Press Release  on Woldiya Massacre

February 1, 2018

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

ወሎ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር:-

"መግለጫና አስቸኳይ ጥሪ"

ጥር 23 ቀን 2010 (January 31, 2018)

የወሎ ጀግና ወጥር ገመዱን፣

ለነጻነትህ ጥረግ መንገዱን! . . . 

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

ከኢትዮጵያ ክ/ሃ ሕብረት ስለወልድያ የአጋዚ ጭፍጨፋ የተሰጠ መግለጫ፦

January 20, 2018

«የሚፈሰው የኢትዮጵያውያን ደም ደማችን ነው!»

የወያኔ መራሹ ግፈኛ ስርዓት በየቀኑ የሚፈጽመው ወንጀል፣ግድያ፣ማቁሰል፣እስራትና ማሳደድ እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አልመጣም።በሥልጣን ላይ የተቀመጠው አምባገነን ሥርዓት ፈራርሶ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ የህዝቧ ጽኑ አንድነትና የዜጎቿ እኩልነት የሚረጋገጥበት ህዝባዊ ሥርዓት እስኪመሰረት ድረስ ትግሉ ይቀጥላል . . . 

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

ከ«ወሎ ውርስና ቅርስ» ስለወቅታዊ የወሎ ፖለቲካ ሁኔታ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ፦

December 13, 2017

በቃ፦ሕዝባችንን ልቀቅ!!

ህዳር 30 ቀን 2010 ዓ.ም.

በሰሞኑ በወልድያ ከተማ የትግራይ እግር ኳስ ቡድን ከወሎ ቡድን ጋር ሊያደርግ የነበረውን ጨዋታ ተከትሎ የተነሳው ብጥብጥ ለአያሌ ሰዎች ህይወት መጥፋትና መቁሰል ለብዙ ንብረት መውደምም ምክንያት ሆኗል።ይህ እስፖርትን ሽፋን አድርጎ በወያኔ ዘበኛ ፈጥኖ-ደራሽ ሃይል ታጅቦ ወደ ቦታው የተላከ የጥፋት ሃይል ገና ከወሎ ድንበር ላይ ሲደርስ ጀምሮ የሕዝቡን ስሜትና ሞራል የሚነካ ፍጹም ብልግናና ድፍረት የተሞላበት የዘር ጥላቻን ያዘለ ስድብና ህገ ወጥ የቁጣ-ቅስቀሳ ተግባር (provocation) እንጂ በእለቱ የተፈጸመ ድንገተኛ ክስተት አልነበረም . . .

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

ከኢትዮጵያ ክ/ሃገሮች ማህበራት የተሰጠ የጋራ መግለጫ

November 4, 2017

በየትኛውም የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ መኖር መሠረታዊ የዜግነት መብት እንጂ በጎሰኛ ፓለቲከኞች የሚሰጥ ችሮታ አይደለም! . . . . . . . . 

~~~~~~~~~~~~~~~~~~

 

"What Studies in Spatial Development Show in Ethiopia," World Bank

አለም ባንክ፦ በኢትዮጵያ ወረዳዎች መካከል ያሉት የእድገት ልዩነቶች

September 24, 2017

{ካርታዎቹ የነሱ፣ ትንተናው የኛ} . . . 

 

 

 

Density of bottom 40% of income  ከደገኛው፣ይሻል ቆለኛው።

Density of bottom 40% of income

ከደገኛው፣ይሻል ቆለኛው።

 

===========================

The Unnoticed 2017-18 Ethiopian Famine is Well Underway

Let us join hands to make famine history!

September 5, 2017

Millions of people in the Horn of Africa are currently facing acute food and water shortages on the heels of a major food crisis in 2015-16.  Whatever the precipitating causes (drought, global warming, etc.), the underlying cause is the unwillingness of sitting governments to guarantee food security in slowly-developing famines become a clear and present danger...

*  *  *  *  *  *  *  *

August 30, 2017

የወያኔ መንግስት የሰሜን ጎንደር ዞንን ለመከፋፈልና የምዕራብ ጎንደርን መሬት ለመቀራመት ያወጣዉ እኩይ እቅድ አገር አጥፊ ነው! ...

*     *     *     *     *

August 9, 2017

ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ሕዝብን እርስ-በርሱ ለማጋጨትና ለማጫረስ በማሰብ በየወቅቱ የቀውስና የችግር አጀንዳ ከማውጣት ቦዝኖ የማያውቀው የጎሠኞች ስብስብ የሆነው ወያኔ መራሹ ቡድን በተለመደ መሠሪ ባኅሪው እነሆ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሁለት አገር የሚያናጉ የጥፋት መንገዶችን ቀይሶ ሕዝባችንን ወደ ትርምስ እየገፋው ይገኛል። ...

*     *     *     *     *

Seattle, July 6, 2017:

 • ስለ 'ወሎ ውርስና ቅርስ' የሰጠነውን ድርጅታዊ ማስተዋወቂያ . . .

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

መግለጫዎቻችንን ሙሉ በሙሉ ለማንበብ "events" ገጽ ሄደው ይመልከቱ።

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

 

 

 

አብይ ተልዕኳችን፦

ዘር-አልባ የክፍላተ-ሓገራት አስተዳደራዊ መዋቅርን በዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ማቋቋም።

==============================

የኢትዮጵያ ክፍለ-ሃገራት ሕብረት፦

https://www.ethiopianhibret.com/

ወሎ ውርስና ቅርስ፦

https://www.wollo.org

ጎንደር ሕብረት፦

http://www.gonderhibret.org/

ጎጃም አለም አቀፍ ትብብር፦

http://gojjamglobalalliance.org/

 

Sheger FM interview on the illustrious historical heritage of Wollo.

መልካም 2011 ለሁላችሁ!! 

===========

Trending:     Ethiopiawinnet! Andnet!

De-trending:     Zeregnet!   Zerafinet!                                         Fisumawinnet! 

==========

ያዲስ አመት መልእክቶቻችን፦

 • የለውጥ ጭላንጭሉን እንደግፋለን፣ ታላቅ ስጋቶችና ምኞቶም አሉን፡፡

 • የሕዝባችን አንድነት ባለቤተኝነትና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በሹም-ሽር አይታደጉም፣

 • የአማራን የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን ሳታዳላ በሙሉ ፍታ፡፡

 • የወልቃይትንና የራያን አካባቢ የአማራ ማንነትንና የዜነት መብት -ይከበር ጥያቄን አስከብር፣

 • የወያኔን ነጭ ለባሽ አስወጥተህ የተፈናቀለው ህዝብ ተመልሶ የራሱን መስተዳደር እንዲያቋቁም አመቻች፡፡

 • ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የከፋፍለህ-ግዛውና የምዝበራ ማነቆህን ያካተተውን የደማሚት ህገ-መንግስትህን ቀደህ አንሳ፣

 • ፍርሃትንና የቅጥር-አበጋዞችን ጭፍጨፋ ወጣቶቻችን አሸንፈዋቸዋል፣

 • የበሰለ ዜጋ ራሱን ለቋሚ ለውጥ ማዘጋጀትን ዘንግቶ ለጊዜያዊ አምባገነኖችና ያንደበት ደላዮች አድኑን እያለ አያጎበድድም፤ ራሱን በኩራት ያድናል እንጅ!

 • ኢሓዴግ  ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ሕዝብ የሆነ ካንሰራዊ ደዌ ነው፣ በጥልቅ ተሃድሶ እንኳ ፍፁም አይድንም!

 • ለ፴ አመታት አካባቢ ላስፈንከው የአረመኔ ስቆቃ ዘመን እግሩ ላይ ወድቀህ ህዝቡን ይቅርታ ጠይቅ!

 • የምንፈልገው ሃቀኛ "መሪ" እንጅ "ተደማሪ" የግል ተጠቃሚ ጀሌን አይደለም!!

ኢትዮጵያ ወዴት?

 • በእርቀ-ሰላም ሂደትም ተዳኝተህ አፋኝና ዘር ተኮር ስልጣንህን ለሕዝብ ተቀባይነት ላለው አገልጋይ ልቀቅ!

 • ስር-ነቀል ለውጥ የሚያመጣ ሁሉን አሳታፊ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር መንግስት ሂደት ይጀመር፣

 • የጥንቱ የክፍላተ-ሃገር መስተዳደርሮች በዘር-አልባነትና በሕዝብ ይሁንታነት ይዋቀሩ!!

 • ከዚህ በኋላ ብቻ ነው ፍትሓዊና አስተማማኝ ውጤት ያላቸው የአካባቢና የፓርላማ  ምርጫዎች ሊፈጸሙ የሚችሉት።

********

በወሎ ህዝብ ላይ ወያኔ ያደረሰውን ታሪካዊ በደል ዝርዝር ለማወቅ እዚህ ይርገጡ፦

*********

Yosef Eshetu.1.20.2018.jpg
WOLLO PROVINCE BEFORE AND AFTER 1991

WOLLO PROVINCE BEFORE AND AFTER 1991

ETHIOPIAN PROVINCES, 1952-1992

ETHIOPIAN PROVINCES, 1952-1992

የወሎ ክፍለ-ሃገር ተወላጆች የሆን ኢትዮጵያውያን እነሆ ታላቅ የታሪክ ዝናን ያተረፈውን ውርሳችንንና ቅርሳችንን ለማዳበርና ለማክበር፣እንዲሁም የወሎን ሕዝብ ህልውና፣ ነጻነትና እድገት ለመደገፍ እንዲረዳ በማሰብ ይህን የሲቪክ ድርጅት አቋቁመናል። እንደውነቱ ከሆነ ወሎ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚኮራባቸው እሴቶች አሏት--የስነ-ሕዝቧ ስፋት፣የጀግኖቿ እምቢተኛነትና፣ጠንካራ የኢትዮጵያ ብሄርተኝነቷን መጥቀስ ብቻ ይበቃል   ** መተዳደሪያ ደንባችንን ለማንበብ እዚህ ይርገጡ **

==========

We, Ethiopians hailing from the historic region of Wollo, hereby establish a civic organization to celebrate as well as to promote our illustrious cultural heritage, and to support the common cause of freedom and development for the people of the region. Our motto, “Wolloyenet is our marker; Ethiopiawinet is our identity” embraces all Ethiopians who cherish our shared history and our aspirations for a democratic Ethiopia. In so doing, we affirm our pride in Wollo and its enviable legacies. Wollo is a model for Ethiopia for its vibrant diversity, for its tradition of defiant resistance against tyranny, and for its unflinching political identification with a united and democratic Ethiopia.             ** Download Our Bylaws **

 

 

=================================

"ወሎ"

[ከአገሬ አዲስ]

ከቶ አይሰለችም ስሙ ቢደጋገም፣

ወሎ ያገር ዋልታ፣ወሎ ያገር ቅመም፡፡

--› ሙሉውን ለማንበብ "FORUM" ገጽ ይህዱ።

 

የወሎ ተስፋ  * ኪነቶቻችን፥ ውርስና ቅርስሶቻችን *

የወሎ ተስፋ

* ኪነቶቻችን፥ ውርስና ቅርስሶቻችን *

February 2018:

The centenary of the death of Ethiopia's premier heroine:

Etege Taitu Bitul.

 

እንደምን ናት ወሎ የቴጌዎች አገር፥

የወንዱ ሲገርመን ሴቱም አይበገር፡፡

 

Ethiopia Hagere 

Ethiopian Music
Korem (1984): A mother's love defeats death.   Food security is a right, not a privilege.   10 ሚሊዮን የቀን ረሃብተኛና 55 ሚሊዮን መሃይም ዜጎችን ያካተተች አገር ታሳፍረናለች እንጅ አታኮራንም፤  ድህነትን ባገራችን የታሪክ አተላ ለማድረግ ድርሻችንን እንወጣ!!

Korem (1984): A mother's love defeats death.

Food security is a right, not a privilege.

10 ሚሊዮን የቀን ረሃብተኛና 55 ሚሊዮን መሃይም ዜጎችን ያካተተች አገር ታሳፍረናለች እንጅ አታኮራንም፤

ድህነትን ባገራችን የታሪክ አተላ ለማድረግ ድርሻችንን እንወጣ!!

ራያ ራዩማ፦ ወሎ ስትመለስ ሁሉም ቦታ ይልማ!!

ራያ ራዩማ፦ ወሎ ስትመለስ ሁሉም ቦታ ይልማ!!

*************************************

ከሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢታዊ ግጥሞች

(1811-1908 ዓም፥ዘብሔረ-ወረሂመኖ፤ ወሎ)

*     *     *     *     *

የከተማ ወንፊት በርበሬ እየነፋ፥
ንፋስ የመጣ እንደሁ ነፊው ዓይኑ ጠፋ፤
ዓይኑን እስከሚያሸው ነፊ አጥቶ ተደፋ፥
ንፋስ እያየ ነው በርበሬ የሚነፋ፥
ፍሬው ካልወደቀ ገለባ አይነፋ::

*      *      *       *

ምን መላ ይገኛል ጦር ቢያከማቹት፣

አልገዛም ካለ ከወንድም ከሴት፤

ሸዋ ካልመከረ ይሆናል ወንፊት፣

እባብ መርዙን ከተፋ ይመጣል ፍጅት፣

ይህን እየሰማህ እንዳትገባ እሳት::

***************************************